ለመብታቸው ጥያቄ በማቅረባቸው የሞት እጣ የደረሰባቸው ኢትዮጵያዊ

         Image0140ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

በሃገሬ ኢትዮጵያ ፧ የፍትህ፤ የነጻነትና ዴሞክራሲ እጦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ችግሩ መፍተሄ እንዲበጂለት በተለያየ ጊዜ ህዝቡ ለመንግስት ጥያቄዎችን ቢያቀርብም ለችግሩ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ተዋቂና አስተባባር ተብለው የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ፤የፖለቲካ አባላትን ሰበብ አስባብ እየተፈለገ  እስር፤ እንግልት፤ ግርፍ ፤ሞት ወዘተ እየተፈጸመባቸው ነው ።

ላለፉት25 ዓመታት የወያኔ መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች አግባብነትና ዘላቂ የሆነ መልስ የተወሰኑ የባለግዜዎች ተጠቃሚነት እየጎለበተ የብዙሃኑ ህዝብ ጥያቄ እየተዳፈነ በመምጣቱ ህዝባችን በደሉን ለመግለጽና ይህ መንግስት እስካለ ድረ ስ ፍትህ፤ ነጻነት፤ዴሞክራሲ የማይታሰብ በመሆኑ ህዝቡ ባለፉት 25 አመታት ውስጥ ችግሮቹ በግዜ ሂደት የፈታሉ ብሎ በትግስት ጥያቄዎችን  በየደረጃው እያቀረበ አመታት ቢቆጠሩም  ለጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ አፈና፤ እስራት፤ ድብደባ ፤ ግድያ እየተባባሱ በመምጣቱ የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል/  የኢትዮጵያ ህዝብ/ ብሶቱን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ ና ስርአቱ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ ሊመልስ የማይችልበት ደረጃ ላይ  የደረሰ በመሆኑ ስልጣኑን ለህዝ ሊያስረክብ ይገባል ፤ በደል ይብቃ ፤በሚል በተለይም ከ 2008 ዓም መጨረሻ ጀምሮ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል ተቃውሞዎች በሰፊው ተካሂደዋል ። ይሁንጂ ለመብታቸው ጥያቄ ለማቅረብና ብሶታቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ አዛውንቶች፤ እማዎራዎች፤ ወጣቶች፤ ምሁራን  ፤ ተማሪዎች፤ ህጻናት ፤የተለያዩ የፖለቲካ አባላት ወዘተ  በየአደባባዪ የጥይት ሰለባ ሆነዋል፧ በቤት ውስጥ በተደረጉ አድማዎችም የገዥውፓርት ወታደሮች በየቤቱ እየገቡ በርካታ በደሎችን ፈጽመዋል እየፈጸሙም ይገኛሉ። የነገይቷን ኢተዮጵያ ተረካቢ ወጣት በየስርቤቱ ታጉረው ወርቃማውን  የወጣትንት እድሚያቸውን በስርቤት እንዲገፉ እየተደረጉ ነው ።

የወያኔ መንግስት የአስቸኴይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ በኴላ ብቻ ከ50 ሽህ በላይ የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል በተለያየ ቦታዎች በሥር ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። እስሩ አሁንም በስፋት  በአማራ ክልልና በኦሮምያ ክልል ተባብሶ ቀጥሏልል፤ ግድያውም በተመሳሳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ይገኛል ። ከ 2008 ዓም መጨረሻ ጀምሮ  በ 2 ወር ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል ብቻ ለመብታቸው ጥያቄ በማቅረባቸው በ ወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ወታደሮች ጥናት በተደረገባቸው ቦታዎች ብቻ 99 እንደተገደሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ብሮጀክት / ETHIOPIA HUMAN RIGHT PROJECT/ በስምና  በቦታ ጭምር ይፋ አድርጔል ይህ ፕሮጀክት በሁሉም የአማራ ክልል ስራውን ተደራሽ አድርጎ  ለማካሄድ ችግር እንዳጋጠመውና ቁጥሩ ከዚህ እንደሚጨምር ተቁሟል።

በጠቅላላው በኢትዮጵያችን በውስን ወራት ውስጥ ብቻ በወያኔ የተገደሉ ንጹያን ሰዎች ቁጥር ብዙ መቶ ሽዎች  እንደሚሆን ይገመታል። ምእራባዊያን ሃገራት  የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ ባነሳው ጥያቄ ምክነያት በአባገነኑ መንግስት እየተገደለ  እንዳለ እየሰሙ ፊታቸውን አዙረውበታል ምክናያቱም ምዕራባዊያን ከራሳቸው ጥቅም አንጻር ብቻ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው።

ስለዚህ በየትኛውም ሃገር የምንገኝ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የኢትዮ ጵያ ህዝብ ስቃይ፧እስራት፤ ሞት እንዲቆም ሁላችንም በጋራ መረባረብ ይጠበቅብናል።ለግንዛቤ ያህል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት በአማራ ክልል ብቻ በአጭር ከቀናት ውስጥ ተገደሉ ብሎ ያወጣውን ዝርዝር የያዘ ሊንክ  ይመልከቱት

https://www.facebook.com/notes/ethiopia-human-rights-project

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: