አገር የማፍረስ መጥፎ ህልም

Image0140ብርሃኔ አሠበ አለሁድረስ

ኢትዮጵያዊነትን የሚክዱ ጭፍን አስተሳሰብ ያላቸው ግለሰቦች መቸውንም ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና  ነጻነት ቅንጣት ያህል የማያስቡና ጭፍን አመለካከታቸውን ጥቂት የነሱን አመለካከት ተሸካሚ በሆኑ ግለሰቦች በማስረጽና አጃቢ ጭምር በማሰባሰብ ደንባራ ፈረሳቸውን ያፏልላሉ።

የትናንት አያቶቻችንና አባቶቻችን ታላቋ እናት ሀገር ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ / አንድነቷ ተጠብቆ እንዲቆይ ዘር፤ቀለም ፤ሃይማኖት ፤ጾታ ሳይለይ በአንድነት ዳር ድንበሯን ላለማስደፈር ከውጭ ወራሪ ሃይል ተፋልመዋል፤ተዋድቀዋል፤ደምተዋ ፤አጥንትና ደም ገበረዋል ፤ የጋራ ደማቸው ጎርፍ ሆኖ ብዙ ወራሪ ሃይልን አስምጧል።  በዚህ ውድ አጥንትና ደም መስዋዕትነት እናት ኢትዮጵያችን በማንም ወራሪ ሃይል ሳትደፈር እስከዚህ ዘመን ቆይታለች ወደፊትም ትቀጥላለች።

በዚህ ዘመን አንድነት ሃይል ሆኖ አለም ወደ አንድ መንደር እየመጣ ባለበት ዘመን በውጭ የሚገኙ አንዳንድ የኦሮሞ ድርጅትና አክቲቪስት ነን ባዮች ኢትዮጵያን እናፈራርሳለን ኢትዮጵያ የምትባል ሃገርን አንግበን ከሌሎችጋር አብረን አንጓዝም በማለት በድፍረት ሰሞሞኑን ይፋ አድርገዋል።  ትላንት ለዚች ሃገር / ኢትዮጵያ  ቅድም አያቶቻቸው አባቶቻቸው በጀግንነት ደም አጥንት ገብረው  የተከበረች ኢትዮጵያን በደም መሃተም ሲያስረክቧቸው እነሱም በተራቸው አንድነቷ የተጠበቀ አንድ ኢትዮጵያን ለመጭው ትውልድ እንዲያስረክቡ ነበር። ያለመታደል ሆኖ የጀግኖች አባቶቻቸውን አደራ በል የሆኑ ልጆች ተፈጥረው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያሴራሉ።

ይህ አላማቸው በምንም ታምር ሊሳካ  የማይችል ቢሆንም ትንሽ ግብዞችን ሊያደናግሩበትና እነሱ ባበዱበት ፈረስ እንዲያብዱ አጃቢ ማሰባሰባቸው አይቀርምና ይህንን የዘቀተ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ግለሰቦችን በጥንቃቄ በመከታተል በኢትዮጵያ  ጉዳይ ምንም አይነት ድርድር እንደሌለ በግልጽ ሊነገራቸው ይገባል።አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት—–እንዳይሆን ነገሩ፤ ባለጌን ባለጌ መባል አለበት።ባለጌን ባለጌ  ካላሉት አያውቅምና  ነገሩማ  ይህ ከባለጌ በላይም የዘለለ ነው።

ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: