በኢህአዴግ ባለስልጣናትና በህወሃት ወታደራዊ ሃላፊዎች የሚፈጸሙ ሙስናዎች ለህዝባዊ ተቃውሞ መነሻ መሆናቸውን አንድ አለም አቀፍ ድርጅት ገለጸ

በኢህአዴግ ባለስልጣናትና በህወሃት ወታደራዊ ሃላፊዎች የሚፈጸሙ ሙስናዎች ለህዝባዊ ተቃውሞ መነሻ መሆናቸውን አንድ አለም አቀፍ ድርጅት ገለጸ
ኢሳት (ጥቅምት 9 ፥ 2009)
በኢህአዴግ የበላይ ባለስልጣናት እና በትግራይ ወታደራዊ ሃላፊዎች የሚፈጸሙ የሙስና ድርጊቶች ህዝቡ በመንግስት ላይ ተቃውሞ እንዲያነሳ እንዳደረጉ በአበይት ጉዳዮች ላይ የሚተነትን አንድ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ገለጸ።
መሰረቱን በእንግሊዝ ለንደን ያደረገው ቻትሃም ሃውስ (Chatham House)፣ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የ4 ብሄረሰቦች ስብስብ ነው የተባለው ኢህአዴግ በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ቁጥጥር ስር ነው ብለው እንደሚያምኑ አብራርቷል።
ባለፉት 25 አመታት እድገት አሳይቷል በተባለው ኢኮኖሚና ለወጣቱ በሚሰጠው ግልጋሎት መካከል ከፍተኛ ተቃርኖ አለ ሲል ያተተው ይኸው ቻትሃም ሃውስ ያወጣው ጽሁፍ፣ የገነፈለው ተቃውሞ በኢህአዴግ ፖለቲካ በተፈጠረው ሙስና መነሻነት መሆኑን አስነብቧል። በተለይም በኦህዴድ ባለስልጣናት መካከል ስር የሰደደ ሙስና ተንሰራፍቷል ያለው ሪፖርቱ፣ የኦሮሞን ህዝብ ይወክላል የተባለው ድርጅት በራሱ ህዝብ የተጠላ እንዲሆን አድርጎታል ብሏል።
ቻትሃም ሃውስ (Chatham House) እንዳለው አሁን የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማለት ህወሃት/ኢህአዴግ በአገሪቷ ላይ ህግና ስርዓት ማስከበር አለመቻሉን በሚገባ መረዳቱን አመላካች ነው ሲል ጨምሮ ገልጿል።
በተመሳሳይ መልኩ፣ በአፍሪካ የፖለቲካ አደጋዎች አማካሪ የሆኑት ዶ/ር አሌክሳድራ ጋድዜላ (Dr. Alexandra W. Gadzela) ከደርግ ውድቀት በኋላ የህወሃት የበላይነት ጎልቶ የወጣበት እንደነበር ናሽናል ኢንተረስት (National Interest) በተባለ መጽሄት ባሰፈሩት ጹሁፍ አስረድተዋል። የፕሬዚዳንቱ ቢሮ ጨምሮ፣ ፓርላማው፣ ማዕከላዊ መንግስት፣ የፋይናንስና ወታደራዊ ተቋማት በህወሃት ሰዎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ቻይና በኢትዮጵያ ላይ በምታሳድረው ተፅዕኖ ላይ ጥናታቸውን የሰሩት ዶ/ር ጋድዜላ በመጽሄቱ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፉ አስነብበዋል።
ህወሃት አሁን የያዘውን የበላይነት አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም ያሉት ዶር ጋድዜላ፣ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ቢሞክሩም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቁጥጥሩ በህወሃት ስር እንደሚቆይ አስረድተዋል። በመሆኑም አሁን በአገሪቷ የተፈጠረው ቀውስ እየባሰበት እንደሚሄድ ምሁሯ በጻፉት ሃተታ አስረድተዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: