መብቱ ያልተጠበቀለት ህዝብ ሲቆጣ የሚያቆመው ሃይል የለም

           መስከረDSC00849000ም 04 /2009

ብርሃኔ አሰበ

መብቱ ያልተጠበቀለት ህዝብ ሲቆጣ የሚያቆመው ሃይል የለም

የኢትዮጵ ህዝብ ለ25 አመታት በገዥው መንግስት/ TPLF/ ሲደርስበት የነበረውን የፍትህ ፣ የዲሞክራሲና ሰበዓዊ መብት

ጥሰቶች መሰረት በማድረግ፤ ህዝቦች ከሃገራቸው የሚገኙ ቁሳዊይና ሰበዓዊ ሃብቶች እኩል ተጠቃሚ ሊሆኑ ይገባል፤ሁሉም የሃገሪቱ ዜጋ መድሎና መገለል ሳይደረግበት በማንኛውም ቦታ እኩል ተጠቃሚ መሆን አለበት፤በሃገሪቱ ሙስና  የከፋ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ መፍትሄ ሊበጂለት ይገባል ፤በሃገሩ ህዝቡ ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ ሊከበርለት ይገባል፤ህዝቦች በሃገራቸው  በየትኛውም ቦታ ሳይፈናቀሉ ሰርተው ሃብትና ንብረት በማፍራት እንዲችሉ ነጻነት ይሰጣቸው ወዘተ በማለት ችግሮቹ እንዲፈቱለት በተለያየ ጊዜ በተናጠልም በቡድንም ለገዥው ፓርቲ  ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷ።

ይሁንጂ TPLF የህዝብን ጥያቄ ገሸሽ በማድረግ ተሃድሶ አደርገን ችግሩን ፈተናል በሚልማደናገሪያ ቃል ሲሸነግለው ቆይቷ ይሁንጅ ትዕግስቱ የተሟጠጠው ና ስርዓቱ ያንገፈገፈው ህዝብ ዛሬ ላይ ከፊቱ መሳሪያ ተደግኖ እየተተኮሰበትና እየሞተ ” ቆሞ ከመሰቃየት እየሞቱ ነጻነት መውጣት” በሚል መሪ ቃል በበርካታ የሃገሪቱ ክፍል ስርዓቱን አንፈልግም በቃን በማለት ትግሉን አጧጡፎታል ። በመሆኑም በዚህ ቀውጢ ቀን ሁሉም አካላት ከህዝብ ጎን በመቆም የድርሻውን መወጣት ግዴታው ነው።

መብቱ ያልተከበረለት ህዝብ ገንፍሎ ሲወጣ ና ሲቆጣ የሚያቆመው ሃይል የለም በመሆኑም የአገሪቱ ሰራዊትም ሆነ ማንኛውም የታጠቀ ሃይል ወደ ህዝቡ መተኮሱን አቁሞ ቆም ብሎ በማሰብ ከህዝብ ጎን  መወገን ይገበዋል።

ብርሃኔ አሰበ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: