አባገነን መሪዎች ከዲሞክራሲያዊ መሪዎች የሚማሩት መቼ ይሆን ?

DSC00849000ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

17/07/2016

አባገነን መሪዎች ከዲሞክራሲያዊ መሪዎች የሚማሩት መቼ ይሆን ?

በህዝብ የተመረጡ ና ለህዝባቸው የሚሰሩ መሪዎች የህዝባቸውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ  ከህዝባቸውጋርየኣጭርና የረጅምጊዜ  የጋራ ዕቅድ በማውጣት የህዝባቸውን ዴሞክራሲያዊይና ሰበዓዊ መብቶች አስከብረው የሃገሪቱ ማህበራዊ ኢኮነሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተገሃድሮት በከፍተኛ ደረጃ እድገት  እንዲያመጡ አልሞ በመስራት ህዝባቸው የእድገቱ እኩል ተጠ ቃሚ እንዲሆን  ይሰራሉ ፤የአገራቸው ሉአላዊነት እንዲከበር ተግተው ይጠብቃሉ።

አባገነናዊ መሪዎች በተቃራኒው የህዝብን ፍላጎት ወደጎን በመተው የራሳቸውን ጥቅምና ምቾት አልመው በስልጣን ላይ ለረጂም ግዜ የሚቆዩበትን ዕቅድና ፖሊሲ ነድፈው በራሳቸው ባህሪ የሚቀርጹትን የአፈጻጸም ስልት የሚያስፈጽሙላቸው አጃግሪዎች በስራቸው በማሰባሰብ የራሳቸውንና አጃቢዎቻቸውን ፍላጎት ታርጌት አድርገው ይንቀሳቀሳሉ እነዚህ በባህሪያቸው የራሳቸው የግል ጥቅም እስካልጎደለ ድረስ የህዝቦች ሰበአዊ ና ዴሞክራሲያዊ መብት ግድ አይሰጣቸውም። ለመብቱ ጥያቄ የሚያነሳን የህብረተሰብ ክፍልን በማሰር፤ በማሶገድ፤ በመግደል የራሳቸውን ስልጣን  በማራዘም የሃገሪቱን ህብታና ንብረት ይመዘብራሉ።

በዴሞክራሲ የሚያምኑና ስልጣን የህዝብ መሆኑን የሚረዱ /የሚገነዘቡ መሪዎች የህዝብ ጥያቄ ካለና  የህዝብ ፍላጎት ካልተመለሰ በህዝብ ዘንድ ቅሬታ ከተፈጠረ የኔ አመራር ለሀገሬ ፤ ለህዝቤ የሚያረካ ስራ ሆኖ አላገኘሁትም በማለት የመረጣቸውን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው የተሻለ አመራር መምጣት አለበት በሚል የተመረጡበትን የጊዜ ገደብ ከማጠናቀቃቸው በፊት ስልጣናቸውን ለህዝብ ያስረክባሉ ይህ የታላቅነት ታላቅ መገለጫ ነው።

አባገነን መሪዎች ግን ህዝቡ  ፍትህ ተጓድሏል ፤ ሰበዓዊይና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተጥሰዋል፤ ሙስና በሃገሪቱ ሰፍኗል፤ህዝቦች ከሃገራቸው ከሚገኝ  ሃብት እኩል ተጠቃሚ አልሆኑም  ወዘተ ስለዚህ አላገለገላችሁንምና ስልጣን ልትለቁ ይገባል ብሎ ጥያቄ ለሚያነሳ ህዝብ ቆምብሎ ከማሰብ ይልቅ እስራት ግድያ ሰቃይ ምላሻቸው ይሆናል። እነዚህ በባህሪያቸው የስልጣን ጥመ ኞች በመሆናቸው የህብረተሰብ  እደገት ሳይሆን የሚያረካቸው ከደሃው ህዝብ ዘርፈው የሚያካብቱት የግል ንብረታቸው ነው።  ለዚህ አብዛኛው የአፍሪካ መሪዎች በአብነት የሚቀርቡ ናቸው። እነዚህ መሪዎች የማገለግለውን ህዝብ ጥያቄ ማርካት አልቻልኩምና  የታሻለ መሪ ሊመጣ ይችላል ብለው ከዲሞክራት መሪዎች በመማር ስልጣናቸውን ለህዝብ የሚያስረክቡበት ጊዜ መቼ ይሆን ?

BERHANE ASSEBE ALEHUDRES

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: