የጎንደር ቀዉስ

የጎንደር ቀዉስ – ግርማ ካሳ
ከሰባት ባላነሱ መኪናዎች ተጭነው ነው፤ በሕወሃቱ አባይ ወልዱ ትእዛዝ ፣ በሰላም የሚኖረዉን የጎንደር ህዝብ ለማሸበር እንደ ወንበዴ በሌሊት የተሰማሩት። አገሪቷ ሕግ አላት ይሉናል። የክልሉ የጸጥታ ሃይል አለ። የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪዎች አሉ። የጎንደር ከተማ የከንቲባው ጽ/ቤት አለ። በጎንደር ሕዝብ ላይ ስለተፈጸመው ምንም የምናወቀ ነገር የለም ነው እያሉ ያሉት። ለምንስ ነው ከትግራይ በትግራይ ክልል መሪ ትእዛዝ ታጣቂዎች የሽብር ወንጀል ሲፈጽሙ ዝም የሚባሉት ? እነ ኮሎኔል ደመቀ እና ሌሎች የወልቃይት የማንንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት ምንድን ነው ያጠፉት ? ጉዳያቸዉን በሕገ መንግግስቱ መሰረት የፌዴሬሽንን ምክር ቤት እንዲመለከተው መማጸናቸው ነው ወንጀሉ ?
እኛ የምናወቀው ትግሬዎች ከሌላው ኢትዮጵያዊ ግአር በመሆን ጎንደር ለምን ተነካች ብለው ሕይወታቸውን ሲሰጡ ነው። አጼ ዮሐንስ ጎንደር በደርቡሾች ስትጠቃ፣ ጦራቸው ወደዚያ አዝምተው፣ ሕዝቡን ለመታደግ፣ በበጌምብድር፣ በመተማ ነው የተሰዉት።
የአሁኖቹ ገዢዎች ግን፣ ጥጋብ ያሰከራቸው፣ የትግራይን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ፣ ግን ምንም ከትግራይ ሕዝብ ጋር የማይገናኙ መንግስታዊ ወንበደዎች ግን፣ ጎንደርን እያመሷት ነው። ወገኖቻችንን እየገደሏቸው ነው። ዳግማሚ ደርቡሾ !!!!!
በአሁኑ ሰዓት የመንግስት ወታደሮች በከተማዋ ቢኖሩም ባንኮችን እና አንዳንድ መስሪያ ቤቶችን ብቻ ነው እየጠበቁ ያሉት። የተቀረው ጎንደር ከአገዛዙ ቁጥጥር ዉጭ ሆኗል። ያለዉን ሁኔታ ለማረጋጋት የቻለ አካል እስካሁን አልተገኘም። በከተማዋ አንዳንድ ቦታዎችም የለየለት ጦርነት እንደተጀመረ ነው የሚነገረው። በርካታ የሕወሃት ደጋፊ ናቸው የሚባሉ ከፍተኛ ፍርሃት ላይ ወድቀዋል። የአንዳንዶቹም ሱቆቻቸዉና ንብረቶቻቸው እየወደሙባቸው ነው። አገዛዙ ህዝብን ካለማክበሩና ችግሮችን ሰላማዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ባለመቻሉ ፣ በዜጎች ዘንድ እየጨመረ የመጣው ንዴትና ምሬት ገንፍሎ ሁኔታዉን ወደ ማይፈለግ ደረጃ እየወሰደው ነው።
አገዛዙ በሌሎች ቦታዎች እንዳደረገው፣ የበለጠ ሰራዊት አሰማርቶ እነ ኮሎኔል ደምቀን ገድሎ ወይንም አፍኖ ፣ “አረጋጋው” ሊል ይችል ይሆናል። ሆኖም መረጋጋት ለመፍጠር ሲሉ የሚወስዱ እርምጃዎች ከፍተኛ የሆነ የደም መፋሰስን ሊያስከትል እንደሚችል ከወዲሁ ላስጠነቅቅ እወዳለሁ። ያው በዘር ላይ የተመሰረተ የደም መፋሰስ።
በመሆኑን ሰዎቹ ቆም ብለው ያስቡ እላለሁ። በአስቸኳይ ከትግራይ ተጭነው የመጡ የሕወሃት ታጣቂዎች ጎንደርን ለቀው መዉጣት አለባቸው። በጎንደርር ለፈሰሰው ደም አባይ ወልዱ ተጠያቂ መሆን አለበት። አፍነው የወሰዷቸውዉን ሌሎች የኮሚቴ አባላት መፍታት አለናቸው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: