በኦሮምያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን በኖኖ -አሎ ቀበሌ በሚኖሩ የአማራ ዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጸ

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በሚፈቅደው መሰረት ዜጎች በሃገራቸው በማንኛውም ቦታ ተንቀሳቅሰው ማልማትና ንብረት ማፍራት እንደሚችሉ ይደነግጋል። ነገር ግን በኢትዮጵያችን  በህገ መንግስቱ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ሲሆኑ አይታይም ይሁን እንጅ ዜጎች ህገ መንግስታቸውን መከታ በማድረግ ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ ሃብትና ንብረት ካፈሩ በኳላ ከሌላ ክልል የመጣችሁናችሁ በሚል በአማራ ብሄረሰብ ላይ በተለያየ አመታት /ጊዚያት ሃብትና ንብረታቸውን በመቀማት እንዲሰደዱ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል/ እየተደረገም ይገኛል

በቅርቡም በኦሮምያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን በኖኖ -አሎ ቀበሌ በሚኖሩ የአማራ ተወላጅ ላይየወረዳ አመራሮችና የቀበሌ አመራሮች ጥቂት ጎጠኞችን በማስተባበር የዚህ ክልል ተወላጆች አይደላችሁም፤የተሻለ ንብርት አፍርታችኋል በማለትየአማራ ተወላጅ የሆኑትን  በረጅም ጊዜ ያፈሩትን ሃብትና ንብረት በሳት በማቃጠል በዚህ ክልል ሃብትና ንብረት አፍርታችሁ መኖር አትችሉም በሚል ከፍተኛ በደል ተፈጽሟል

እንደንዚህ ያሉ አመራር ነኝ ባዮች የልማትና የእድገት እንቅፋቶች ሃገር ሲለማ የሚያማቸው፤ ሰው ሰርቶ ሲለወጥ አይናቸው የሚደማ  ከንቱዎች፤ ጎሰኝነትና ዘረኝነት የሚያስፋፉ ጎሳን ከጎሳ  በማጋጨት እድሚያቸውን የሚያራዝሙ የሃገር ሸክም ናቸው።ተጠያቂነት ሲጠፋ ሁሉም የመሰለውን ና በዘፈቀደ ህግና ደንብ ሳይጠበቅ ውሳኔዎችን በመሰለው ይወስናል እየሆነ ያለውም ይህው ነው ምክነያቱም ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ በግፍ የማፈናቀል ተግባር የፈጸሙ አመራሮች ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ዛሬም በግፍ ማፈናቀሉ ተፈጽሟል። ለማናኛውም መሉ ዝርዝሩን ሰ መ ጉ የተሰኘው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅትሪፖርትያዳምጡ http://amharic.voanews.com/content/article/2915312.html

ብርሃኔ አሰበ

Leave a comment