ይቺናት ምርጫ ! 100% ማሸነፍ

ሰኔ 16/2007

በ ብርሃኔ አሰበ

ይቺናት ምርጫ ! 100% ማሸነፍ

ትክክለኛ ምርጫ በሚደረግባቸው ሀገራት ህዝቦች በራሳቸው ተነሳሽነትለመራጭነት በመመዝገብና የተለያዩ አማራጭችን ይዘው የሚቀርቡ ፓርቲዎች አማራጫቸውን /አላማቸውንና ግባቸውን/ ለህዝብ በነጻነት በማስታዋወቅ በዚያች ሀገር ላይ የሚገኙ ህዝቦች ያለምንም  ተጽዕኖ የተሻለ አላማና ግብ ይዞ የሃገሪቱን/ቷን/ ኢኮኖሚያዊይና ማህበራዊ ችግሮችን የሚፈታ ፤ የሃገሪቱን ሉአላዊነት የሚያስጠብቅ፤ ለህዝቦች ነጻነትና ፍትህን የሚያሰፍን ፓርቲን ያለምንም ተጽእኖ በነጻነት ሲመርጡ ይታያል።

ነገር ግን በኢትዮጵያችን የምርጫ ታሪክ ውስጥ ህዝቦች አማራጭ ቀርቦላቸው ህዝቡ ይበጀኛል ያሉትን በነጻነት መምረጥ ህልም ሆኖ ቀርቷል። የዚህ አመት የ2007 ዓም ምርጫ ከምንግዜውም በባሰ አፈና የነበረበት የውጭ ታዛቢዎች ያልነበሩበት፤ የተቃዋሚ ፓርቲ ከመነሻው ጀምሮ  የታሰሩበትና የተገደሉበት፤ ገዥው ፓርቲ በሚፈልገው መንገድ ለመጓዝ ጥርጊያ መንገዱን ለራሱ ምቹ በማድረግ በሁሉም የምርጫ ክልሎች  የፓርላማ  ተመራጩ ሙሉ በሙሉ 100% ገዥው ፓርቲ እንዲሆን ቀድሞ በመወሰንና ይህንኑ ተግባራዊ በማድረግ የ 5 ዓመት ኮንትራቱን በራሱ አጽድቆ አውጇል ።

እውን እውነተኛ በህዝብ ድምጽ ላይ የተመሰረተ ምርጫ ተካሂዶ አንድ ፓርቲ 100% በማሸነፍ ያሳካ ሃገር በአለማችን ይኖር ይሆን ? የህዝብን ድምጽ በመቀማት 100% የአሸናፊነት አዋጅ ያወጁ አባገነን መሪዎች ያሉበት ሃገርን ሳይጨምር ማለቴ ነው።ይቺ ናት! የወያኔ ምርጫ ፈተናውን ሳይሰሩ 100 /መቶ/ መድፈን ፤ ነገ የህዝብ በደል ሲበዛ መንደሩ ሁሉ የራሱን ፓርላማ መስርቶ አባገነናዊ  የሆነውን ፓርላማ በመበታተን በህዝብ የተመረጠ ህዝባዊ ፓርላማ ይተካዋል።

http://amharic.voanews.com/content/ethiopia-election-2007-outcomes-and-implications-crossfire-voa-alula-kebede-06-27-15/2839917.htm

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: