የ 2007 ዓም የኢትዮጵያ ስሌት የለሽ ምርጫ

Image0140_1

ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

የህዝብ ድምጽ የሚያከብሩና የህዝብን ስሜት የሚያዳምጡ መንግስታት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በምርጫ እንዲሳተፉ ና ይዘውት የተነሱትን አላማ ለህዝብ በማስታዋወቅ ህዝብ ይጠቅመኛል ፤ማህበራዊይና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቼን ይቀርፍልኛል፤ለሃገር እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወትልኛል፤ ሰብዓዊይና ዴሞክራሲያዊ መብቴን ያስከብርልኛል የሚለውን ፓርቲ በነጻነት እንዲመርጥ የምርጫ ሜዳውን ምቹ ያደርጉለታል

ነገር ግን በኢትዮጵያችን  ያለው የምርጫ ታሪክ ብዙ አሳዛኝ ክስተቶችን ጥሎ ያለፈነው። በየ 5 አመቱ የሚመጣው የይስሙላ የኢትዮጵያ ምርጫ ከግዜ ወደ ግዜ እየዘቀጠ የሚሄድና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በተለያየ መንገድ ከውድድር ውጭ በማድረግ አንድ ፓርቲ/ገዥውፓርቲ/ ብቻውን ለምርጫ እየቀረበና የመቆያ ግዜ ላይሰንሱን በራሱ እያደሰ የግዜ ቆይታውን እያራዘመ ይገኛል።

ከአመታት በፊት ለይስሙላ በተቋቋመው ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተመዘገቡና በጠበበም እድል ውስጥም  ቢሆ ን ለውድድር ይቀርቡ ነበር።  በምርጫውም ለመሳተፍ የሚደርስባቸውን ልዩ ልዩ ተጽኖዎች ተቃቁመው በምርጫው በመሳተፍና የህዝብን ይሁንታ በማግኘት ወያኔን በማሸነፍ አስደናቂ ውጤት ያገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማሸነፋቸው በየቆ ጠራው ጣቢያ ሲታዎቅ ገዥው ፓርቲ፦

1 / የህዝብን ድምጽ በመቀየር

2/ የውጤት ኮረጆ በመስረቅና ውጤትን በመቀየር

3/ በተሸነፈባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ምርጫው በድጋሜ እንዲካሂያድ በማድረግ በግዳጅ ህዝቡ ኢህአዴግ/ወያኔን እንዲመርጥ በማድረግ

4/ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ውጤት ታዛቢዎችን በመደልል/በማሶገድ/ለራሱ በማስመዝገብ የህዝብን ድምጽ በሃይል ሲቀማ  እንደቆ የ የቅርብ ግዜ ትውስታችን ነው። ከዚህ ጋርምተያይዞ ድምጻችን ሊሰረቅ አይገባውም በሚል ጥያቄ ያነሱ ወጣቶች፤ አዛውንት፤ምሁራን፤ ተማሪዎ ች ወዘተ ተገድላዋል፧ ታስረዋል፧ ተሰደዋል እ ነ ዚ ያ ምርጫዎች የማይረሳ አሳዛኝ ክስተትን አስመ ዝግበው አልፈዋል።

በዚህ አመት የ 2007 ዓም ምርጫን ኢህአዴግ ብቻውን ለመዎዳደር ሽርጉዱን ተያይዞታል የዚህ አመቱ ደግሞ ከምርጫው በፊት አስገራሚ ክስተቶችን እያሰማን ነው ። ይሕም በምርጫ ቢወዳደሩ በአሸናፊነት ይወጣሉ ብሎ ያሰባቸውንና ያሰጉትን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫ በፊት ማሶገድ በሚለው ፕሪንሲፐል ወያኔ  በራሱ አምሳል የቀረጽው ምርጫ ቦርድ በሚሰጠው ቀጭን ትእዛዝ መሰረት በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ታመኔታ ያላቸውንና ጠንካራ የሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ምርጫው እየተቃረበ ሲመጣ እውቅና ያልነበራችሁ ናችሁ፧ምርጭ ፖርድን አታከብሩም ወዘተ ወዘተ በሚል ያልተገባ ምክነያት የፓርቲ ፈቃዳቸውን በመሰረዝ እንዲበተኑ አድርጓል።

የፓርቲ እውቅናው ከመቀማት/ከመሰረዝ / ና ከመበተን በቀዳዳው ሾልኮ ያመለጣቸው እና በጠንካራ ወጣቶች የተገነባው የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎቹን ለህዝብ ካስተዋወቀና ለምርጫው እጩዎቹን ካስመዘገበ በኋላ በርካታ ተከታይ መኖሩን ሲረዱ  እጩዎቹን ካስመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ ሁሉ ከውድድር ውጭ ለማድረግ ሰበብ አስባብ እየተፈለገ አይን ባወጣ ሁኔታ እየተሰረዙ ይገኛሉ።ይህ የሚያሳየው ገዥውፓርቲ ያለምንም ተቀናቃኝ ተቃማሚ ፓርቲ የ 2007 ዓም ምርጫን በአምሳሉ ካደራጃቸው  አጋሮቹ ጋር ተወዳድሮ 100% አሸነፍን የሚለውን ስሌት የለሽ የምርጫ ውጤት ሊነግረንና ለተጨማሪ 5 ዓመት ላይሰንሱን በራሱ አድሶ እንዲህ ነው ምርጫ ! ሊለን ሸርጉዱን አጧጡፎታል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: