የፍትህ እሳቢ በወያኔ ሥርዓት

                      

               BY Hana Geleta

አሁን ኢትዮጵያ ትመራበታለች የሚባለው የኢህአዴግ ህገ መንግስት በመግቢያው ላይ እንዲህ የሚሉ  ወርቃማ ህግጋትን አስቀምጧል። በህጋዊ አገዛዝ ሊይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ለመገንባት በመቁረጥ፡ ይህም የሚሳካው የግለሰቦችና የቡድኖች መሰረታዊ ነጻነትና መብት ሲጠበቅ መሆኑን አምነን፡ (አሁንም ይሄ መሰረታዊ መብትና ነጻነቶች የሚለው ቃል ተደጋግሟል) ይህንን ህገ መንግስት አጸደቅን ይላል።ሆኖም ግን ግፈኛውና ዘራፊው የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ መሬት ከሚሰራቸው ትልልቅ  ወንጀሎች አንዱና ምናልባትም ዋነኛው በህግና ሕገ­መንግስት ላይ የሚያካሄደው  ቀልድና ጭዋታ ነው። 

ሕገመንግስት ህዝብን ከእብሪተኛ መንግስት መጠበቂያመሳሪያ መሆኑ ቀርቷል።  ወያኔና አፋኝ ስርአቱ ህግ የሚጠቅሱት ለራሳቸው  ይጠቅመናል ባሉበት ሰዓት ነው። ህግ ለነሱ ካልተመቻቸው ተቀዶ የሚጣል ቆሻሻ  ወረቀት ነው።    በኢትዮጵያ ምድር ዋናው ሕገወጥ ተቋም ራሱ ላወጣው ሕግ የማይገዛው ወያኔ/ህወሃት ነው። ለዚህ ነው “ለሚመለከተው አካል ከማሳወቅ ውጪ ሰላማዊ ሰልፍ  ለማካሄድ  ፈቃድ  አይጠየቅም”  የሚለውን  ራሱ  ያወጣውን  ህግ  ጥሶ ሰሞኑን ተቃዋሚዎችን ቁም ስቅላቸውን የሚያሳያቸው። ለዚህም ነው ሃሳብን በጽሁፍና  በቃል ለመግለጽ ቅድመ ምርመራ እና እገዳ አይኖርም ብሎ ጽፎ፣ አለም አቀፍ  የሰበአዊ መብት ድንጋጌዎች እንዳሉ ተቀብያለሁ ብሎ የተናገሩና የጻፉ ሰዎችን  የሚያሳድደውና በሽብርተኝነት የሚከሰው።   

 ወያኔ ይህን ለህግ  ትልቅ  ክብር  ያለውን  የህዝባችንን  የዘመናት  እምነት  ድራሹን  በማጥፋት  ላይ  ይገኛል።  ዛሬ በየፍርድ ቤቱ የሚከናወን አይን ያውጣ አሰራር እና የህወሃት  ጀሌዎች እየፈጸሙት የሚገኘዉ በደል የንጽሀን መብት ያለግባብ በመርገጥ ላይ ይገኛል። ፍትህ እና ፍርድ ቤት  እንዲዋረድ ሆኗል። ፍትህና ዳኝነት ራሱ በህወሃት የታሰረበት ጊዜ ነው።አ መት ኣልፎ ኣመት በተተካ ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ ህይወት ይበልጥ ኣስጊ እየሆነ መጥቷል፥ በጦርነት በሚፈጁ ፌደራሎች ኣጭበርባሪዎች በሆኑ ፖለቴከኞች፣ግብዝ በሆነ የሀይማኖት መሬዎች፣ተነሳሽነትና ኣቅም በጎደላቸዉ ወይም ባነሳቸዉ የህግ ባለሙያወች፣ምግባረ ብልሹና ሙያዊ ስነ ምግባር በጎደላቸዉ  ጋዜጣኞችና ርህራሄ በጎደላቸዉ ወንጀለኞች ተሞልታለች፥

በኣጠቃላይ በኢትዮጵያ ላይ ያለዉ የዜጎች የመብት ረገጣ ፣የኣገር ማጥፋት፣ዜጎችን የማፈናቀል፣የዘር ማጥራት፣የመሬት ነጠቃና ኣሳልፎ ለባድ ኣገር ለረጂም ኣመታት በመሸጥ ኢትዮጵያነትን ማጥፋት፥ ዘረኝነትን በማጉላት ኣንድን ብሄር ከፍ ኣድርጎ በመኮፈስ ሌላኛዉን ዘር ሙሉ በሙሉ እንደ ሂትለር እየተከተሉ በፕሮግራም ማጥፋት፥ በተፈጥሮ ሃብትና በኣካባቤ እየደረሰ ያለዉ ጥፋት፣በታሬካዊ ወይም በባህላቅርስ የደረሰዉ ውድመት፣በሃይማኖቶች ጣልቃ በመግባት ኣገረቷ ባህሏንና ሃይማኖቷን ጠብቃ እንዳትኖር ኣድርጔል፥በፍትህ እጦት ሳቢያ በየእስር ቤቶች እየተሰቃዩ ላሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፤ ከማሳዎቻቸው ተፈናቅለው ለተበተኑ ወገኖታችን፤ አደገኛ የበረሃና የባህር ጉዞ በማድረግ ለተሰደዱ ወገኖቻችን፣ ለራሳችን እና ለመጪው ትውልድ ልንደርሰት ይገባል። ፍትህን ከተቀበረችበት ጉድጓድ በቶሎ ካላወጣናት አገር አይኖረንም፤ እኛም ሰዎች ሆነን አንቀጥልም  የፍትህ ጉዳይ  ከህግና ከማኅበረሰብም በላይ ሰው ከመሆናችን እውነታ ጋር የተሳሰረ ነው። ፍትህ በሌለበት ሰው ሆነን መፈጠራችን ዋጋ አይኖረውም። ለዚህም ነው የፍትህን ጥያቄ

ከሰብዓዊ መብትና ክብር ተያይዞ የሚቀርቡት። ፍትህንና ሰብዓዊ ክብርን መለያየት አይቻልም። ሰው ሰብዓዊክብሩን ከቁሳዊ  ምቾት በላይ ይፈልገዋል፤ ይህ ማለት ደግሞ ፍትህን በቁሳዊ ምቾት በላይ ይፈልገዋል ማለት ነዉ። ሰው በሰውነቱ ነፃነትን ተላብሶ የሚመጣ እንደሆነ ሁሉ ከፍተኛ የፍትህ ስሜትም ተላብሶ የሚመጣ ፍጥረት ነው። አምባገነን ገዥዎች

እኛ ባወጣነው ህግ እናንተ ተገዢዎች እንጂ እኛ ገዢዎች አንገዛበትሲሉ እና ከሰው ባህርይና ተፈጥሮ ጋር የሚጣሉ ኢፍትሃዊ ህጎችን ሲያወጡ የህግን መርህ ብቻ እየጣሱ አይደለም፤  በስብእናችን ከእነሱ ያነስን፣ እንዳሻቸው ሊያደርጉን የሚችሉን ፍጥረቶች መሆናችንን እየነገሩን ነው።ወያኔ የሚያወጣቸውን ህጎች ሲፈልግ በሥራ ላይ የሚያውላቸው፤ ሳይፈልግ የሚተዋቸው በመሆኑ የህጎች መኖር ምንም ፋይዳ እንዳይኖረው አድርጓል። በተለይ ከልካይ ህጎቹ ተቀናቃኞቹን እንጂ ራሱን ወያኔን አይከለክሉትም።

ዛሬ አገራችን ውስጥ ያለው የህግ ችግር የመጥፎ (የኢፍትሃዊ) ህጎች መብዛት ብቻ አይደለም። ችግራችን ከዚያም ያልፋል። ባጠቃላይ ህግ የለም፤ ዳኝነት የለም። ህገአልባነት ህግ ሆኗል።   ወያኔ በሥልጣን ላይ በከረመ መጠን የኢትዮጵያ ሕዝብ በፍትህ እጦት የሚደርስበት መከራ እየጨመረና እየመረረ በመምጣቱፍትህ አጣን፤ የፍትህ ያለህየሚሉ እሮሮዎች ከቀድሞው በበለጠ መልኩ እየጎሉ መጥተዋል። በሙስሊም ወገኖቻችን የተቃውሞ ሥርዓቶች እና ሕዝብ እሮሮዉን በትንሹም ቢሆን ለመግለጽ በቻለባቸው መድረኮች ሁሉ ገንኖ የሚወጣው ጩከትየፍትህ  ያለህየሚል ነው። የፍትህ እጦት ነው ወገኖቻችንን በገዛ አገራቸው ተፈናቃይ ያደረጋቸው። የፍትህ እጦት ነው ገበሬዎች ማሳቸው ለባዕዳን ሲሰጥ አንጀታቸው እያረረ ዝም እንዲሉ የሚያደርጋቸው፤ የፍትህ እጦት ነው ነጋዴዎች ሱቆቻቸው በእሳት ሲጋዩ  “ጉዳዩ  ይጣራልን”  ማለት እንኳን ያላስቻላቸው።ኢትዮጵያን በዘር በሀይማኖት በጎሳና በተለያዪ መንገዶች በመከፋፈልና በማናቆር እድሜዉን እያራዘመ የሚ ገኝዉ ዘረኛዉ የወያኔ መንግስት ላለፉት23 ኣመታት በስታሊናዊ የደህንነትና  ወታደራዊ ሀይል ኢትዮጵያ ኣገራችንና  ህዝባችንን በጉልበት ኣፍኖ እየገዛ ይገ ኛል፥በተለያዪ ተቌ ዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶ የሲቪክ ማህበራት ዉስጥ ወያኔ ሰርጎ በመግባትና የራሱን ተለጣፊ በማቆቋም በየግዜዉ እንዳይለመልሙ ከጎናቸዉ ሆኖ ይመነጥራቸዋል፣ኣንዳንዶችም የፖለቲካ ድርጅቶች እንደስራ ማግኛና መጠቀሚያ በማድረግ ህዝብን ከማወናበድ ኣልፈዉ የወያኔን እድሜ በማራዘም ወያኔ እንደፈለገዉ ረግጦ እንዲገዛና  የውጭዉን ሽፋን በማሰመር ላይ ይገኛሉ፥

በኣጠቃላይ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሁሉንም ቅጣቶች  እየፈጸመ  ይገኛል   ስለዚህ  ሁላችንም በኣንድላይ ሆነን በልበሙሉነት ሳንከፋፈል ሰባኣዊ ክብራችን እስኪጠበቅልን፤መብቶች እስከሚከበሩልን፤እኩልነት እስኪረጋገጥልንና ፍትህ እስኪሰፍንልን ድረስ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እዉን እንዲሆን ያለማቌረጥ   እጋፈጥ

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: