የህዝብን ብሶት በመሳሪያ ሃይል ማገት አይቻልም

0 1/04/2007

የህዝብን ብሶት በመሳሪያ ሃይል ማገት አይቻልም

 

Image0140_1 ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

ህዝቦች በአገራቸው ላይ ሰብዓዊይና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተከብሮላቸው ሃሳባቸውን በነጻ መግለጽ ሲችሉ በመንግስትና በህዝቦች መካከል መተማመን ይፈጠራል፧ ለአገርልኡላዊነት በጋራ ይቆማሉ፧ሀገሪቱን በአስተማማኝ ሁኔታ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ለማላቀቅ በጋራ ይተማሉ፧ለለውጥና እድገት ይነሳሳሉ።

በሌላ መልኩ ደግሞ የህዝቦች/ የዜጎች/ መሰረታዊ እሴቶች የሆኑት ሰብዓዊይና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ዝግ በሚሆኑበት ጊዜ በህዝቦችና በመንግስት መካከል በጥርጣሬ መተያየትን፤ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ድህነትን ለመቅረፍ የሚደረግ ትግልን ያቀጭጫል።በአሁኑ ስዓት በኢትዮጵያችን ሰብዓዊይና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ከመቸውም በበለጠ በከፍተኛ ደረጃ እየተጣሰ የምትገኝባትሃገር ሆናለች በመሆን ዜጎች ነጻነታችውና መብታቸው  እንዲከበርላቸው በተለያየ ጊዜ ጥያቄዎቻቸውን  ይመራኛል ለሚሉት አካል/ መንግስት/ ሲያቀርቡ ይደመጣሉ ይሁንጂ ወያኔ /ኢህአዴግ ዜጎቸ ለሚያነሧቸው ጥያቄዎች መፍትሄ በመስጠት ለጋራ እድገትና ልማት ከማነሳሳት ይልቅ  የተለያየ ምክነያትን በመፈብረክ አምራቹን ዜጋ በየስር ቤቱ ማጎርን ስራየ ብለው ይዘውታል።

የዜጎች መሰረታዊ እሴቶች የሆኑት ሰብዓዊይና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ሲጓደሉባቸው በተናጠላም ሆነ በጋራም ብሶታቸውን በግጥም፧ በቅኔ፧ በጽሁፍ፧ በተለያዪ ሚዲያዎች ለመንግስታቸው ይገልጻሉ።ከዚህ ሲያልፍም ችግሮቻቸውን በጋራ ሆነው ድምጻቸውን በአደባባይ ያሰማሉ።

በአገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ስአት ህዝቦች ያለባቸውን ማህበራዊይና ኢኮኖሚያዊ፧ ሰብዓዊይና ዴሞክራሲያዊ ችግሮቻቸውን በሰለጠነ አግባብ በአደባባይ ድምጻቸውን ለማሰማት በሚወጡበት ስአት  የህወሃት/ወያኔ መንግስትን የተለያየ ስያሜን በመስጠት ንጹህ ህዝቦችን፧የተቃዋሚፖለቲከኞችን፡ጋዜጠኞችን — ወዘተ ሰብአዊይና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በመጨፍለቅ ኢሠበዓዊ የሆነ ድርጊት እየፈጸመባቸው ይገኛል ለዚህም  በሰሞኑ እየሆነ ያለውን መጥቀስ በቂነው ይኸውም በሰላማዊ መንገድ  የመብት ጥያቄ በማንገብ አደባባይ በመውጣት ላይ የነበሩ ህዝቦችን በመደብደብና በማሰቃየት በስር ቤት በማጎር ላይ ይገኛል ከዚህም በዘለለ በፀረ አሸባሪ ህግ ሽፋን ንጹህ ዜጎችን ለመብታቸው በመታገላቸው ብቻ  አሸባሪ በሚል  ፈሊጥ ለመወንጀል ሲጣደፍ ይታያል።

የኢህአዴግ/ ህወሃት መንግስት ለሃገርና ለህዝቦች ጥቅም ከመቆም ይልቅ ፧የህዝብ ብሶትን/የሃገሪቱን ዜጎች ችግር ከማዳመጥና ከመቅረፍ ይልቅ ግለሰባዊ የፓርቲና ቤተሰባዊ ጥቅምን በማስቀደም የብዙሃኑን መብቶችና ጥቅሞች ሲያዳፍኑት ይታያል።

የኢህአዴግ/ ህወሃት መንግስት ፀረ ህዝባዊነት አቋሙን ይበልጥ እያገዘፈ  በመምጣቱ ህዝቦች ማህበራዊይና ኢኮኖሚያዊ፧ ሰብዓዊያና  ዴሞክራሲያዊ ችግሮቻቸውን በአደባባይ በሰላማዊ ሰልፍ ድምጻቸውን ማሰማት እንደሚችሉ በህገ መንግስቱ የተቀመጠላቸው መብት ቢሆንም የተቀመጠው ህግ ለይስሙላ እየሆነ  ከመቸውም በበለጠ በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ኢሠብአዊ የሆነ ድርጊት እየፈጸመ ይገኛል።

ነጻነቱን ያጣ ህዝብ ሊውል ሊያድር እንጂ አንድ ቀን ሁሉም በጋራ ገንፍሎ አፋኝ ስርዓትን በአጭር ግዜ ውስጥ የሚያሽመደምድ መሆኑን በአለማችን ላይ በቅርብ የታዩ የህዝብ የአደባባይ አመጾችን ማስታወስ በቂ ነው።በኢትዮጵያ ህገመንግስት ላይ ሰብዓዊይና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ መሆናቸው የተደነገገ ቢሆንም  በአገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች ሰው በመሆናቸው ብቻ የማይጣሱትና የማይገፈፉት ሰብዓዊይና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ከምንግዜውም በላይ እየተጣሱ ያሉበትወቅት ላይ በመሆናችን ይህንን አስከፊና ከጊዜ  ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የሰበአዊ መብት ጥሰት የመብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች፧የተለያዪ የፖለቲካ ድርጅቶች ፧ ሲቪልመሃበራት፧የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወዘተ ሁለገብ በሆነ መልኩ በጋራ በመንቀሳቀስ ልናስቆም ይገባናል።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: