«የግራዛኒ ልጆች ነን ፤የባንዳ ልጆችነን ብንል ኖሮ ተሸልመን እንገባ ነበር»

መጋቢት 16 /2006

Image0140_1   ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ/BERHANE ASSEBE ALEHUDRESS

ለዚህፁሑፍመነሻየሆነኝ ሃሳብማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገውየሴቶች 5 ሺህኪ.ሜሩጫውድድርላይ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት እንስቶች የነጻነት ቀናቸውን ተጠቅመው ብሶታቸውን በአደባባይ ጮክብለው አሰምተዋል። ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው፤ ይህ ቀን ሴቶች ተሰባስበውና ተጠራርተው ለነፃነታቸው ቀደምት ሴቶች ያደረጉትን ተጋድሎ በመዘከር ያሁኖቹ ሴቶች ለበለጠ እኩልነት እና ነፃነት በጋራ የሚቆሙበት የቃል ኪዳን ቀን ነው፡፡ ይህንን በውል የተረዱት የኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ስለነፃነታቸው ከፍ ባለ ድምፅ ሲዘምሩ ታይተዋል። እነዚህ ወጣት ሴቶች ስለነጻነታቸው በልበ ሙሉነት ጥያቄ ማንሳታቸው በማንኛውም ወገን ሊበረታቱና ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚገቡ የነገ ሃገር ተረካቢ የብጽል ጣይቱ ራእይን የሰነቁ እንስቶች ናቸው። ይሁንጅ ገጅው መንግስት ለነጻነታቸው ያነሱትጥያቄ ቆምብሎ በማሰብ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ የተለያየ ስያሜ በመስጠት ድብደባ ፤ እንግልት፤እስራት አደረሰባቸው።

እነዚህ ወጣትሴቶች የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ብሶታቸውን በሰላማዊ መንገድበማንጸባረቅ ነጻነት እንፈልጋለን፤ ፍትህ እንፈልጋለን ፤የፖለቲካ እስረኞችይፈቱ፤ ጋዜጠኞችይፈቱ፤ነጻ ኢትዮጵያን ይፈቱ፤አትከፋፍሉን ኢትዮጵያ አንድናች— ወዘተ በማለት በነጻነታቸው ቀን ስለነጻነታቸው ያለባቸውን የውስጥ ችግራችውን ጥያቄ ማንሳታቸው እስርቤት ያሶረውራቸው ነበርን? እስከመቸስ ነው ለነጻነት ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ወደ ስርቤትየሚወረወሩት? እስቲ ይህንን ቪዲዮ ተመልክተው ፍርዱን ይስጡ

VIDEO https://www.facebook.com/photo.php?v=1427012600879046

Image

ርዕሴን የመረጥኩት በሩጫው ላይ ከተሳተፉትና ቃለ መጠይቅ ከተደረገላት ወጣትየተነገረው ቃል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊወያዩበት የሚገባ አነጋጋሪ አረፍተ ነገር ይሆናል ብየ ስላሰብኩኝ ነው ። ይህንን ነበር ያለችው  » እኛ የጣይቱ ልጆችነን፤ እኛ የምኒልክ ልጆችነን በማለታችን ታሰርን ነገርግን የግራዛኒ ልጆችነን፤ የባንድ ልጆችነን ብንል ኖሮ ተሽልመን እንገባ ነበር« ነው ያለችው የሁላችንንም ህሊና የሚፈታተን ቃል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የግራዛኒና የባንዳ ተግባር የኢትዮጵያን ህዝቦች በእጅጉ የጎዱ የኢትዮጵያ ዋና ጠላቶች ናቸው።

በ19ኛው ክፍለ ዘመን የሴቶች አመራር ሰጭነት በአለማችን ብዙም በማይታይበት በዚያን ዘመን በልሂቱና በአመራር ሰጭነቷና የሃገሯን ሉአላዊነት በማስከበር አውሮፓን ያስደመመች የብጹል ጣይቱን እና በእውነተኛ ኢትዮጵያን ዘንድ ምንጊዜም ሲታወሱ የሚኖሩት እምየ ምኒልክን በማንሰት«እኛ የጣይቱ ልጆች ነን፤ እኛ የምኒልክ ልጆችነን « የነገ የሃገር ተረካቢ ሴት ወጣት የጣይቱን ተግባር ለመፈጸም ዝግጁ የሆንን ተተኪ ትውልዶች ነን ማለታቸው ለእስራት፤ ለእንግልት ከዳረጋቸው እውነትም የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላትየሆኑት ስም እያነሱ የግራዛኒ ልጆችነን፤ የባንዳ ልጆችነን ቢሉ ኖሮ በወያኔ መንግስት አበጃችሁ ተብለው ሊሞገሱ/ሊሸለሙ የሚችሉ መሆኑን አይጠቁምም ትላላችሁ። እነዚህ ወጣት ሴቶች ያነሷቸው የፍትህ፤ የነጻነትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች እውን እስከሚሆኑ ድረስ ከጎናቸው ለንሰለፍ ይገባናል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: