ያንየ «ዲቪ» . . . ወደ ኢትዮጵያ ነበር።

1

የስዯት ሕይወት የዛሬው ኢትዮጵያዊ ትውልድ መታወቂያ ከመሆኑ በፊት ሇኢትዮጵያውያን ክብራችን መሇያችን፣ መሇያችንም ክብራችን ነበር። ከእግዚአብሔር የተሰጠን ኢትዮጵያዊ ጸጋ በግድም ሆነ በውድ ከእኛ ከመራቁም በፊት ዜግነት ምን እንዯሆነ ጠንቅቀን የምናውቅ የክብር ባሇጸጐች የነበርንበት ዘመን ነበረ። አሇመታዯል ሆኖ ነዉራችን ክብራችን እየሆነ መጣ እንጂ ኩሩዎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች የአገራቸውን ጥቅም የማያስነኩበት፣ ክብሯን የማያስዯፍሩበት የቃል ኪዲን ዘመንም በድሮ ጊዜ ነበረ። እንዯዛሬው በዏረቡ ዓሇም ኢትዮጵያዊ እንዯ ሰው ሳይሆን እንዯ እንስሳ በግፍና በጭካኔ ከመዋረደ በፊት ሇዜጐቹ ዯህንነት የሚሟገት መንግሥትና ተከብረው የሚያስከብሩ መሪዎችም በተከታታይ የታዩበት ዘመንም ነበረ። በእንግድነት የመስተናገድ ክብር ያላየው የዛሬው ትውልድ ከመፈጠሩም በፊት ሇዘመናት እንግዲ ተቀባይ ሆና የኖረችው ኢትዮጵያ የውጭ አገር ሰዎችን በሥርዏት ታስተናግድ፤ ከዚያም አልፎ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ሇሚፈልጉ ዯግሞ ዕድለን ትሰጥ ነበር።
ነበር።
ከዛሬ አንድ መቶ አንድ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት አውጥቶት የነበረውን አንድ አዋጅ ስንመሇከት የዛሬውን ውድቀታችንን ከበፊቱ ማንነታችን ጋር ሇማነጻጸር ይረዲን ይሆናል። ማነጻጸር ብቻም ሳይሆን ወዯቀዯመው ክብራችን ሇመመሇስ የሚያስችለንን እርምጃዎች እንድንወስድ ያነቃቃን ይሆናል ብዬ አስባሇሁ። በቋንቋችን ላይ እየዯረሰ ያሇውን መበላሸት ከመግታት ጀምሮ በፈሪሀ እግዚአብሔር የታነጸ ትውልድ እስከመገንባት ድረስ ሃላፊነቱ የእኛው ነው። ቸልተኛነታችን እየጐዲን ጊዜውም እየረፈዯ ነው። ስሇሆነም በጥቂት በጥቂቱ እየተሸረሸረ ያሇው ኢትዮጵያዊነታችን ጨርሶ ከመጥፋቱ በፊት መንቃት ይጠበቅብናል። «ነበር»ን የመቀየሪያው ጊዜ አሁን ነው።
ወዯጠቀስኩት አዋጅ ልመሇስ። በብልሁ፣ በአስተዋዩ፣ በጥበበኛው፤ ሕዝብ ፍቅሩንና አክብሮቱን የሚገልጽበት ቃል ቢያጣ «እምዬ» እያሇ ይጠራቸው በነበረው በታላቁ መሪያችን በዲግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የወጣ አዋጅ ነበር። ወዯ ኢትዮጵያ በጉብኝትም ሆነ በሥራ የሚገቡትንና በወቅቱ ቁጥራቸው እየጨመረ የነበረውን የውጭ አገር ሰዎች በሥርዏት ሇማስተናገድ ታስቦ የወጣ አዋጅ ነበር። እንዯሚከተሇው ይነበባል፤
አዋጅ
እስከዛሬ ድረስ ቆንስለ ሳይታወቅ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ብዙ ዓይነት የውጭ አገር ሰው አሇ። ስሇዚህ ካሁን ቀዯም በሌጋሲዮኑ መዝገብ
2
ያልተጣፈ የውጭ አገር ሰው ሁለ ቆንስለን አስታውቆ በሌጋሲዮኑ መዝገብ
ይጣፍ።
ቆንስል የሌሇው ግን እንዯዚህ ቀዯሙ ያሇ ቆንስል አዱስ አበባ መኖር
አይችልምና ስሇዚህ የሚያድርበትን ቆንስል ሇይቶ ያስታውቅ።
ዯግሞ ቆንስል ሳይኖረው ቀርቶ ዜግነቱን ወዯ ኢትዮጵያ መንግሥት
ማድረግ የሚፈልግ ሰው ግን ይኸንኑ ዜግነቱን ወዯ ኢትዮጵያ መንግሥት
ማድረጉን የሚፈቅድሇትን ወረቀት ከመንግሥቱ ተቀብሎ ካመጣ በኋላ
እንዯዯምቡ ከኢትዮጵያ መንግሥት መዝገብ ይጣፋል። እንዯዚሁም ቆንስለን
አስታውቆ በሌጋሲዮኑ ወይም በኢትዮጵያ መንግሥት መዝገብ ሇመጣፍ
ከዛሬ ጀምሮ እሶስት ወር ድረስ ቀን ሰጥተናል። ከዛሬ ጀምሮ እሶስት ወር ድረስ
እንዯዯምቡ ከመዝገብ ሳይጣፍ የቀረ ሰው ግን የኢትዮጵያን መንግሥት ሇቆ
መውጣቱ የታወቀ ይሁን።
ግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፭ ዓመተ ምሕረት አዱስ አበባ ተጻፈ።
የኢትዮጵያን የወዯፊት ዕድል፤ የዛሬውንም ኢትዮጵያዊ ስዯትና ውርዯት ስናስብ ይህንን
ከአንድ መቶ አንድ ዓመታት በፊት የወጣውን የግንቦት ሀያ አዋጅ እናስታውሳሇን።
እያስታወስንም ይህንን የስዯት፣ የውርዯት፣ የክፍፍል፣ የክሕዯትና የውድቀት ዘመን ድል
ሇመምታት በአንድነት እንነሣሇን . . . «ነበር»ም ይቀየራል፤ ኢትዮጵያም ወዯቀድሞ ክብሯ
ትመሇሳሇች። ምኞቴም እምነቴም ይኸው ነው።
_______________
ቴዎድሮስ አበበ
የካቲት ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. │ February 19, 2014
ዋሽንግተን ዱሲ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: