ስብዕና የጎደለው መሪ

የካቲት06/06/2006

  Image0140_1 BERHANE ASSEBE ALEHUDRES/ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ/

አንድ መሪ እመረዋለሁ የሚለውን ህብረተሰብ የተጠየፈበትና ሊጠየፍ የሚችልበት አግባብም ሊኖር አይችልም።አንዳንድ አባገነንና የበታችነት የሚሰማችው ግለሰቦች ስልጣንን በተለያየ መንገድ እጃቸው ካስገቡ በዃላ የወጡበትን ህብረተሰብ/ የሚመሩትን ህብረተሰብ/ሲጠየፉት፤ሲያዋርዱት፤ ሰብዓዊ ክብሩን ሲጋፉት፤በድህነቱሲሳለቁበት ይሰማል።

በቅርቡ በኢትዮጵያችን የአማራ ክልል ምክትል መስተዳድርና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አላምነው መኮንን እመረዋለሁ የሚለውንና በማንነቱ የሚኮራውን የአማራ ህብረተሰብ እጅግ አስቀያሚና ህሊናን ሊጎዳ የሚችል የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱበት ሰማን!

አማራው- ስናፍጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናዎተው

– በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግርየሚናገር

-የትምክህት ልሃጩ መራገፍ ያለበት —– ወዘተ አመራር ተብየው ይህንን በማንነቱ የሚኮራ ህዝብ ለማሸማቀቅ፤በሌሎች ብሄሮች እንዲጠላ፤በጠላትነት እንዲታይ ፤ ከሌሎችጋር ተባብሮና ተከባብሮ እንዳይኖር በአደባባይ ሰበዓዊ ክብሩን የሚነካ ስድብ በመሳደብ በድህነቱ ሲሳለቅበት ይሰማል።

ውዱ የሃገሬ ህዝብ በባዶ እግሩ ቢሄድ አንዲትም አሳፋሪ ተግባር የለውም ። በባዶ እግሩ እንዲሄድ ያደረጉት አላምነው መኮንንና መሰሎቹ ሆነው እያለ ዛሬ ይዘባበቱበታል ፤አላምነው መኮንን በባዶ እግሩ ይሄዳል ብሎ ከሚሳለቅበት ህብረተሰብ በሙስና በሚዘርፈው ገንዘብ እየተንደላቀቀ ለመስማት የሚያስጠይፍ  የባለጌ ስድብ ሲሳደብ ራሱን ከሌላ አለማት የመጣ የተለየ ፍጡር አድርጎ የሚቆጥር የዘቀጠ አስተሳሰብ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው።

«ኩራት ራት ነው» ብሎ እንደ አመራሮቹ ሰርቆ ከመክበር በባዶ እግር እየሄዱ ራስን መቻል ብሎ አፈር ገፍቶ የሚያድረው አርሶ አደር የሃገሬ ኩራት እንጅ ማፈሪያና መሳለቂያ አይደለም፤ በባዶ እግሩ ያለጫማ እየሄደ የሃገሩን ሉአላዊነት ያላስደፈረ ኩሩ ህዝብ እንጅ  ልጓም በሌለው በለጌ አፍ የሚሰደብ፤ የሚሽሟጠጥ ፤የሚዘለፍ፤የሚንቋሸሽ አይደለም።

በኢኮኖሚ ችግር ምክነያት በባዶ እግሩ እንዲሄድ የተገደደው የአማራው አርሶ አደር በባዶ እግሩእየሄደ  በሚያመርተው ምርት የሚንደላቀቁት መሪዎች ራሱን ጎድቶ ሆዳቸውን በሞላ ለምን ይሆን በጠላትነት የሚያዩት? የአማራውን ህብረተሰብ በተለያየ ስልት ማንነቱን ለማሳጣት ከሚኖርበት የተለያየ የሀገሪቱ ክፍል ያፈራውን ሃብትና ንብረት ትቶ እንዲፈናቀልና ቤተሰቡ በረሃብ እንዲቀጣ፤የነገ ሃገርተረካቢ ልጆቹ በዜግነታቸው ማግኘት የሚገባቸውን የትምህርት እድል ተረጋግተው እንዳይማሩ ሲደረግ፤ መሬቱን እየተነጠቀ ለሌላ ባዕድ ሀገር ሲከለል ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ፍትሃዊ የሆነ ምላሽ የሚሰጠው አጥቶ ዝም ቢል ደልቶትና ተቀብሎት ሳይሆን አመራርህ ነን ተወክየለሃለሁ የሚሉት በሚያደርሱበት ጫና «እስከሚያልፍ ያለፋል» በሚለው የሃገሬው ብሂል የሆዱን በሆዱ ይዞ ዝም ማለቱን አላዋቂነት ቆጥረውት ይሆን?ይህ መሪ ተብየ የአማራውን ህብረተሰብ የሚያንቋሽሽ የጥላቻ ቃላት/ስድብ/ በውስጡ ሰንቆ የኖረውን በዚህ አጋጣሚ የልቡን የተነፈሰ የህወሃት ተላላኪ ነው።

የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ እንዲሉ የክልሉ መስተዳደር ፕሬዘዳንት አቶ ገድሉ አንዳርጋቸው የምክትላቸውን አባባል ለማስተባበል በማይገናኝ ትንታኔ ለማለት የፈለገው የክልሉን ልማት ለማፋጠን መግባባት፤በአንድነት መንቀሳቀስ ያስፈልገናል ለማለት የተጠቀመበት አግባብ ነው ይሉናል። ቅምዝምዝ ወዲህ ጥንቸል ወዲያ የሆነ መግለጫ። በባዶ እግሩ የሚሄድ ድሃ አርሶ አደር፤ነገረኛ አማራ፤ ልሃጫም አማራ  ወዘተ ወዘተ አንድነትን የሚያጠነክሩ ፤ለልማት የሚያነሳሱ የአማራውን ብሶ ት/ ችግር/ የሚያሳዩ ልማታዊ ቃሎች መሆናቸው ነው?ይህ ብቻ መቸ በቃ አላምነው መኮንን በአማራው ክልል የአርሶ አደሩ ሂዎት እንዲለወጥ ሌት ከቀን ሲባዝን የቆየ አሁንም ሌት ከቀን እየሰራ የሚገኝ አመራር ነው ብለውን አረፉ።ይህ የሚያሳየው እውነትን ለመሸሽና ጥፋተኛ ስለሆነ ለህግ ይቀርባል የሚል ድፍረትን በማጣት በአደባባይ የተባለን አድበስብሶ ለማለፍ የተደረገ የማይገናኝ መግለጫ ነው።

ይህ በአማራው ህዝብ ላይ ያፌዘ ፤ያላገጠ፤ያናቋሸሸና ሰበዓዊ ክብሩን የደፈረ ግለሰብ በህግ ሊጠየቅ ይገባዋል ለዚህም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ሌላውም የህብረተሰብ ክፍል ለህግ ቀርቦ እንዲጠየቅ የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው።

 

 

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: