ማንዴላ ታላቅ ሰው! ከመ/ጥ መንገሻ መልኬ

ጥቁር ሰው ተንቆ ፤ሲታጨድ ሲወቃ፤
እንደ እንስሳ ሆኖ ፤ተረግጦ እንደ ጭቃ፤
ማንዴላ ተነሳ የነጻነት አባት ታላቁ ጠበቃ፤
ካፋፍሎ መቀጥቀጥ ከእንዲህ አበቃ!።

በእጁ ጥይት ሳይኖር፤ ቦንብ ሳይወረውር፤
ክፋታን ሳያስብ መጥፎ ሳይናገር፤
ብቻውን ጠበቃ፤ ብቻውን ምሥክር፤
በጥበብ ሰበረው የጭቆናን ቀንበር፤
ገዳይ ተገዳዩ በፍቅር በማሰር።

የነጻነት አባት የአንድነት ዘበኛ፤
የጥቁር ሰው ኩራት የአመጸኛ ዳኛ፤
ማንዴላ ታላቅ ሰው የሰላሙ አርበኛ።

ማንዴላ ታላቁ የነጻነት አባት፤
የስምምነት ሰው የእርቅ መሠረት፤
ቦንብ ሳይወረውር፤ ሳይተኩስ ጥይት፤
ቂም በቀል ሳያስብ፤ ሳይኖረው ክፋት፤
ተገዳይ ገዳዩን ጠበቀው በአንድነት።

ፋገግታው ያማረ ታላቅ የሰላም ሰው፤
መብትን ጠባቂ ሕግን አስከባሪ ለተበደለው፤
ጥቁርና ነጩ ተቻችሎ እንዲኖር ለዓለም ያስተማረው።

ማንዴላ ታላቅ ሰው የሰላም ሐዲድ፤
እሥርቤት ሳይገታው የጭንቀት ወጥመድ፤
የዘመኑ አርበኛ ለሚመጣው ትውልድ፤
በአንድነት ተፈታ በፍቅር ገመድ።
ከመ/ጥ መንገሻ መልኬ
የጭቁንኖች ልሳን የሰላም አለኝታ፤
ጉልበት ለሌላቸው ጋሻና መከታ፤
ሰላሳ ዓመት ታስሮ እንዲያ ሲንገላታ፤ (27)
ሁሉንም በፍቅር ቻለው በፈገግታ፤
ማንዴላ ታላቅ ሰው የአንድነቱ ዋልታ።

ማዴላ በስደት ኢትዮጵያን ጎበኛት፤
የነጻነት ቀንዲል ምድሪቱ ያች! ናት፤
እራሱን አንቅቶ መልኩን ያየባት፤
ለዚህ ታላቅ ክብር ምክር ያገኘባት።

ኢትዮጵያ ሰው ይስጥሽ ፤ሰው እንደ ማንዴላ፤
በዘር የማይከፍል ለፍቅር ለአንድነት የሆነ ከለላ።

ሰው እንደ ማንዴላ፤ ኢትዮጵያ ሰው ይስጥሽ፤
የእውነት ምስክር ሕዝብ የማይከፋፍል የሚጠብቅሽ፤
አድልዖ የሌለው ሰው ቂም በቀል ሰርዞ የሚያስታርቅልሽ።

በወንጌል ያመነ ፤ በሱ የተመራ እሱን ያማከረ፤
የሰላሙን አዋጂ ለዓለም ያበሰረ፤
የዘር መከፋፈል በትግል ያስቀረ፤
ለተጭቆነው ሕዝብ መብት ያስከብረ፤
ለሀገሩ የሠራ ማንዴላ ታልቅ ሰው በቃ ተቀበረ።

ማንዴላ ታላ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: