አቦይ ምን ገዷቸው !

አቦይ ምን ገዷቸው እሚግደረደሩ፤
በሰላማዊ ሰልፍ አገር ቢያማረሩ፤
በክረምት ተቃውሞ ዜግነት ቀየሩ፤
በአሜሪካን ምድር በቅንጦት ሊጦሩ፤
በመስከረም አጥቢያ ባህር ተሻገሩ፤
በአገር በቀል ሰላይ ባንዳ እየተመሩ፤
ፊታውራሪ ስብሃት ዲያስፓራን ወረሩ።

ዘር ከልጓም ስበው እየተጠራሩ፤
ጸጋዬ በርሄ፤ቴውድሮስ አድሃኖም፤ኢሳያስ ባህሩ፤
‘አይሲሲ’ን አፍረሰው ደሳለኝ ሊበሩ፤
የመለስ ወራሾች በራዕይ ያደሩ፤
ልማታዊ ስደት ሰሞኑን መከሩ፤
ዲያስፓራን ‘ጠርዘው’ ምርኮ ወደ ሃገሩ፤
የደደቢት ሽፍቶች በዲሲ ሊሰፍሩ፤
እኛን ሲዖል ጥለው በገነት ሊኖሩ።

ወገን ተጠራርተው በወኔ ፎከሩ፤
ለጨበጣ ውጊያ ስንቅም ባይቋጥሩ፤
በሜሪላንድ፤ዲሲ፤ በቨርጅኒያ ጦሩ፤
ሃያት ሲከበቡ ‘ስታርባክስ’ አደሩ፤
በጥፋታቸው ሱስ አገር ሲያሸብሩ፤
አቦይ ስብሃት ብርክ አቀረቀሩ፤
በዓለም አደባባይ በቁም ተደፈሩ፤
በቅምጥ ተጨርሰው ሊሸኙ እንደ እድሩ።

ጀግናው ጋዜጠኛ ፃዲቅ ሞገታቻው፤
አንገት አስደፍቶ አርበተበታቸው፤
በገለጡት ገጽ ላይ አፍጦ አበሳቸው፤
የያዙት ጋዜጣ አትንካኝ ሲላቸው፤
ፀሃፊውን አስረው ማንበብ ተሳናቸው፤
ሳልና ውጋቱ አጣድፎ አስነሳቸው።

ደግሞም በማግስቱ ጨበጣ ተያዙ፤
በባንዳ ታጅበው አድፍጠው ሲጓዙ፤
ድንገት ያገኛቸው የነፃነት ታጋይ፤
ሞገታቸው በቁም መስፍን በአደባባይ፤
የአገሩን ደመኛ የወገኑን ገዳይ፤
ፊልም እየቀረጸ ነግ ለዓለም እንዲታይ።

በአንክሮ ሲጠይቅ እዳ አበሳቸውን፤
አክ ብሎ ተፉብን ምራቁን፤ ለሃጩን፤
ቅልብ ጡንቻው ቡጢም አያሳረፈብን፤
አስር ሺህ ማይል ርቀን እዚህም ተሰደን፤
ወያኔው ስብሃት ከቶ አስዘመተብን፤
አዋርዶ፤ አወራርዶ ሰውም አላረገን፤
እስኪ ካሁን ወዲያ ትዕግስታችን ይብቃን፤
ምላሽ እንደግስ ሕግ አገር ይፍረደን፤
እጃችን ይቅመሱ ፈትፍተን፤ ጠቅልለን፤
እንቁላል፤ ሚጥሚጣ ሁሉንም መጥነን።

ማስታወሻ፡
ሰሞኑንና ለወደፊትም ማፊያውንና አገር አፍራሹን፤
ሕዝብ ጨራሹን የወያኔውን ቡድን በድፍረት
ለሚያሳደዱና ለሚጋፈጡ አገር ወዳድ
ኢትዮጵያዊያን ምስጋና ትሁንልኝ። የጐንቻው!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: