ጽናት

ደም ሊያፈስ፤ ሕይዎት ሊቀጥፍ አደባባይ ባሰፈሰፈ፤
ሺህ ጭምብላም አስጀንጅኖ ባለቆመጥ ካሰለፈ፤
ከምድር አፈር ተንበርክኮ በአቋም ጽናቱ የገዘፈ፤
ለሰንደቁ ፍርሃትን ገፎ የድፍረት ሸማ ደርቦ ያጎናጸፈ፤
ሳይሸበር፤ ሳያሸብር ጀግናው ወጣት ፊት ደረቱን የሰየፈ፤
ቀናዒ ለእምነቱ በሶልዖት ስጋጃው ቃል ኪዳኑን ያነጠፈ፤
አንብንቦ በልቡ የሞት ሠራዊትን አሞት በፍላጻ የነደፈ፤
ታልቅ መልዕክት በአንዱ ሳተና ፊትና ግምባር የተጣፈ፤
ደዎል ነጋሪት ግፍ ከልክ አልፎ የሕዝብ ማዕበል እንደጐረፈ፤
በባዶ እጁ፤በባዶ እግሩ፤ አዲስ ገድል፤ዓውደ ምዕራፍ የፃፈ፤
ሺህ የምድር አሽከላ፤ በኢድ አጥቢያ አንዱ ሰማያዊ አሸነፈ።
በፍርፋሪ ከደለቡት በደም በዘር ከሰከሩት፤
ዘዎትር ቀን ለጥፋት በጐጥ መንደር ከሚንጋጉት፤
ነጋ ጠባ የሰላም የቅዱሳንን ጉባዔ ከሚያውኩት፤
ጸብ ጫሪዎች በደም ክርፋት ከሚረኩት፤
በኢትዮጵያዊ አበሳ ወያኔ ከሃዲውን ካነገሱት፤
ክፉ አጋዚ መልዓከ-ሞት ምዕመናንን ከሚገድሉት፤
በቁጣ የወረደ የሰማይ ክፋይ የምድር ቦቀልት፤
ተጋፈጣቸው በአደባባይ በምድር በሰማይ ፊት ለፊት፤
አንዱ አሳቻ፤ በሶልዖት የቁርጥ ቀን የድል ብስራት፤
አንጥፎልናል የነጻነት መሰረት፤የወደፊታችን መስተዋት፤
የዘመን፤ የትውልድ ቋጥኝ፤ የመንፈስ፤ የጽናት ሃውልት።
አንዱ ጀግና ሺህ የሚመከት እጡብ ድንቅ አርዓያ የነጻነት፤
እንዲህ ነው ወንድም! የአቡበክር፤ የእስክንድር አርነት፤
የአንዷለም፤የበቀለ፤የርዕዮት፤የውብ እሸት፤ጥሪ ከወህኒ ቤት፤
ዘጠና ሚሊዮን የቁም እስረኞች፤የሚሰቃዩ ሃያ ዓመት በግዞት፤
እንከተል የአንዱን ጀግና ሪቂቅ ምስጢር የሶልዖት፤የፆም ጸሎት፤
የሕልውናችን ማብሰሪያ የስጋና የመንፈሳችን እሥሥራት፤
የሃገር፤ የዜግነት፤ የደም፤ የሥጋ የእትብት ቁርኝት፤ አንድነት፤
እንዘይር እስልምና፤እንዘክር ክርስትና ኢትዮጵያዊ ድንቅ ጽናት።
ፍርሃት በነገሰበት ዘመን፤ ለታደጉን እንደ ቅርጣን፤
ለብርቅዬ ጀግኖቻችን፤ ገድል መታሰቢያም ትሁን!

የጐንቻው! yegonchaw@yahoo.co.uk
16.08.2013

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: