የህወሃት/ወያኔ መንግስት የኢድአልፈጥር በዓል የደስታ መግለጫው የንጹሃንን ደም በማፍሰስ ይሆን?

የህወሃት/ወያኔ መንግስት የኢድ አልፈጥር በዓል የደስታ መግለጫው የንጹሃንን ደም በማፍሰስ ይሆን?

Image0140_1

ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ

ኢትዮጵያ ከምትታዎቅባችው ውድ ቅርሶቿ መካከል አንዱ የተለያዩ ሃይማኖቶች/እምነቶች ባለቤት መሆኗ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ቀደምት አባቶቹ ያወረሱትን እምናቶችና ሃይማኖቶች ይዞ በመከባበርና በመተባበር እየኖረ ያለና ጽኑእምነቶቹም የሃገሩን ልኡዓላዊነትበማስከበር ረገድ ትልቅ ሚና እንደነበራቸውታሪክ ይመሰክራል። በሌላ መልኩም ህዝቦች ለመልካም መሪዎቻቸው ለመገዛት ስልጣን የእግዚአብሄር ነው በእግዚአብሄር ካልተቸር በስተቀር ስልጣን የለምና (በክርስቲያን አማኞች ዘንድ)፣ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ መለዕክተኛውንና ከናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ (በእስልምና እምነት ዘንድ)—,የሚለውን የየእምነታቸውን ቱርፋት መነሻ በማድረግ ለመልካም መሪዎቻቸው/ ለህዝብ አሳቢ ባለስልጣናት/ ተገዥነትን ወይም ትህትናን ያሳዩ እንደነበረ ጥናቶች ይጠቁማሉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሃገር ከሌለ ሃይማኖት የለም፣ የሃይማኖት መከባበር ሃገርን ያስከብራል፣ሃገርንያስጠብቃል። የሚል ጽኑ እምነት አለው። በተቃራኒው ሲተገበር ደግሞ በሃገር ላይ የሚያመጣውን ምስቅልቅል ችግር ጠንቅቆ ያውቃል።ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ህዝብ በሃይማ ኖቱ ጉዳይ ለድርድር የማይቀርበው ፣ለዚህም ነው በእምነቱ ጉዳይ የሚመጣበትን ለመጋፈጥ ወደ ኋላ የማይለው፣ለዚህም ነው በእምነታችን ጣልቃ ሊገባብን አይገባም ብሎ በየስርአቱ አጥብቆ  የሚሟገተው። ይሁን እንጂ እንደ የስርአቱ የተለያየ መልክ ቢኖረውም የኢትዮጵያ እምነቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ የሆኑበት ጊዜ የለም። ለዚህም ዋነኛው ምክነያት ገዥዎች በሃይማኖት ከለላ የግዞት ጊዜያቸውን ለማራዘም የሚቀይሱት ዋነኛ እስትራቴጅ መሆኑን ጥናቶች ያመለክታሉ። በተለይም አባገነናዊ መንግስታት ሃይማኖትን በከፋፍለህ ግዛ እስትራቴጃቸው አንደኛው ሃይማኖት ሌለኛውን በጥርጣሬ እንዲመለከተውና ተባብረው በአገዛዙ/በመንግስት/ ላይ ጥያቄ እንዳያነሱ በሚቀይሱት ዘዴ እድሜአቸውን ማራዘም ዋነኛ ስልታቸው ነው።እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ደግሞ በሃይማኖት ላይ ጣልቃ ገብነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቶ እንሆ በኢትዮጵያችን በዚህ ዘመን የሃይማኖት መሪዎችን/አባቶችን/ የሚመርጠው የሃይማኖቱ ተከታይ ህዝብ ሳይሆን መንግስት እየመረጠ የሚሾምበትና ለእምነትነጻነት ጥያቄ የሚያነሱ አካላትን አሸባሪ በሚል ለእስርና ጭካኔ ለተሞላበት ድብደባ የሚዳረጉበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ለአብናትም -በዚህ ሰሞን የ 1434ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ለማክበር በወጣ ንጹሃን የእምነቱ ተከታይ ህዝብ ላይ ለዚያውም እናቶችና አዛውንት አባቶች ላይ የደረሰው የዱላ ውርጅብኝ ና ኢሠበአዊ ድርጊት ከጣልቃ ገብነትም አልፎ  አረመኔያዊ ድርጊት ሆኗል።    

የህወሃት/ወያኔ መንግስት የ1434ኛ የኢድ አልፈጥር በአል የደስታ መግለጫው የንጹሃንን ደም በማፍሰስ ይሆን?      

   ዘጋጅ  ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ     

       10/8/2013  

Advertisements

3 thoughts on “የህወሃት/ወያኔ መንግስት የኢድአልፈጥር በዓል የደስታ መግለጫው የንጹሃንን ደም በማፍሰስ ይሆን?

  1. አቶ ብርሃኔ በጽሁፍህ ጥሩ መወያያ የሚሆን ጥያቄ አቅርበሃል በኢትዮጵያችን ለዲሞክራሲ፣ለእምነት ነጻነት ማንሳት ህወሃት/ወያኔ
    የህዝቦችን ጥያቄ ፣ ጥያቄ ነውብሎ ከማሰብና ፍትሃዊ መልስ ከመስጠት ይልቅ አሸባሪ የሚል ስም በመስጠት ንጹሃንን ህዝብ መጨፍጨፍ
    የእየለት ተግባሩ ሆኗል።ይባስ ብሎ ህወሃት/ወያኔ ለእስልምና እምነትተከታይ ህዝብ የኢድአልፈጥር በአል የደስታ መግለጫውን ደም በማፍሰስ አስተናግዶታል።
    እነዚህ ገዳይ የሽፍቶች ስብስብ ነገ እነሱም የእጃቸውን ያገኛሉ።

  2. TPLF/WEYANIE ongoing arrests,killings&beating of innocent people of Ethiopians. So we Ethiopians to integrate & struggle for
    justice, democracy & freedom

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: